Course Hive
Search

Welcome

Sign in or create your account

Continue with Google
or
Emerging Technology Fresh man course : Big Data ,cluster computing በአማርኛ ሙሉ ማብራሪያ
Play lesson

Emerging Technology fresh man course - Emerging Technology Fresh man course : Big Data ,cluster computing በአማርኛ ሙሉ ማብራሪያ

4.0 (1)
14 learners

What you'll learn

This course includes

  • 3 hours of video
  • Certificate of completion
  • Access on mobile and TV

Summary

Keywords

Full Transcript

📍A- Atomicity: ይህ በዳታ መሃል የሚፈፀሙት "transactions" ወይ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ ይሆናሉ ወይ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ይከሽፋሉ። ግማሹ ተቀያይሮ ግማሹ ደግሞ እንዳይቀር የሚያደረገው "Atomicity" ሲይስተም ነው። 📍C- Consistency: ensures that a transaction can only bring the database from one valid state to another. ይህ "transaction"ኡ/ ልውውጡ በሚፈፀም ጊዜ የዳታው ትክክለኝነት (correctness) እንደተጠበቀ መሆኑን የሚቆጣጠረው ወይም የሚያረጋግጠው የConsistency ባህሪ ነው። 📍I- Isolation:  ensures that concurrent execution of transactions leaves the database in the same state at the same time. "transaction"ኦቹ በተመሳሳይ ሰዓት እና ሁኔታ እየተፈፀሙ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ነው። (ማለትም ተራ በተራ እንዳይፈፀሙ ያንን ነገር የሚያስቀር (Isolate የሚያደርግ) ነው። 📍D-Durability: guarantees that once a transaction has been committed, it will remain committed. አንድ ጊዜ የተፈፀመው "transaction" ቶሎ የሚጠፋ ሳይሆን የሚቆይ ነው፥ እናም ያንን መቆነቱን (durable መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።) 5⃣Data Usage: It covers the data-driven business activities that need access to data. ይህ የመጨረሻው የተከማቸውን ዳታ አውጥተን በተለያዩ ነገሮች💵⚖ ተግባራዊ እያደረግን የምንጠቀምበት ደረጃ ነው። 📓Big Data 📌What is Big Data❓ 'ትልቅ ዳታ' የሚባል ነገር አለንዴ🤔 የሚል ጥያቄ ተፈጥሮባችሁ ይሆናል። ነገር ግን 'Big Data' ማለት ብዙ የዳታ ስብስብ ሆኖ እኛ ቀድሞ በምናውቀው መንገድ (በወረቀት ላይ ወይም በአንድ ኮምፒዩተር ራሱ ሆኖ በተለመደው መንገድ ኮምፒዩተሩ ላይ ጭነን ለመጠቆም ከባድ የሆነ የዳታ አይነት ነው። ይሄ ዳታ የተሰበሰበው ከተለያየ ምንጭ ነው (ከዚህ በፊት እንዳየነው ከአንድ ምንጭ (Source) ብቻ አይደለም (ለምሳሌ ከExcel file💻 ብቻ አይደለም) ከተለያዩ Pdfኦች🧾፣ ከተለያዩ ቪድዮ📷💾 እና ፎቶዎች፣ Emailኦችም ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ: የማህበራዊ ድህረ ገፅ ዳታ፣ በባንክ ቤት የምንጠቀማቸው ዳታዎች (Transaction processing systems), ትላልቅ የሞባይል አፖች (Mobile Apps),... 🌻Big Data is: 📍Large Datasets (ትልቅ የዳታ ስብስብ ነው) 📍The category of computing strategies and technologies that are used to handle large datasets. (እነዚያን ብዙ እና ትላልቅ የዳታ ስብስቦችን አስልተን ለመጠቀመ የሚረዱንን ቴክኖሎጂዎች በውስጡ የያዘ ነው።) 🌻Characteristics of Big Data 📌Big Data is mainly characterized by 3V: ከሌሎች የዳታ ስብስቦች (Other data Systems) "Big Data System" በዋናነት በሚከተሉት ነገሮች ይለያል። 1⃣Volume: refers to the amount of data. በ"Big Data" ውስጥ የሚገኘው የዳታ መጠን የሚገልፅ ነው። 2⃣Velocity: refers to the speed of data processing. በዳታው ውስጥ የሚገኘው መረጃ (information) በምን ያክል ፍጥነት ነው በሲይሰተሙ ውስጥ የሚሄደው። 3⃣Variety: refers to the number of types of data. ቅድም እንዳየነው በ"Big Data"ው ውስጥ የሚገኙ ዳታዎች የተለያዩ አይነት እና ከተለያዩ ምንጮች የተገኙ ናቸው። (ከፎቶ📷፣ ከኢሜይል፣ ከተለያዩ ዶኩሜንት📑...) "Big Data" የሚገለፀበት ዋና ባህሪያቱ እነዚህ ናቸው። በእርግጥ የተወሰኑት ተጨማሪ አሉ። 📍Veracity: ከእውነታ ጋር ያለው ስምምነት ማለት ነው - ማለትም በ'Big Data' ውስጥ የሚገኙት ዳታዎችን፦ Accuracy, Quality & Trustworthiness (ታማኝነት) የሚያሳይ ነው። 📍Value: እያንዱንዱ በ'Big Data' ውስጥ የሚገኘው ዳታ ዋጋ እንዳለው (የሚጠቅሙ መሆናቸውን) የሚያሳይ ነው። ኮምፒዩተሮች (Individual Computers) በ"Big Data" ውስጥ የሚገኙት ዳታዎች መቆጣጠር ስለማይችሉ፥ እዛ ውስጥ የሚገኘውን ዳታ ለመቆጣጠር ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው "Computer Cluster" የተባለውን ዘዴ ነው። ምን ማለት ነው❓ "is a set of computers that work together so that they can be viewed as a single system." 📓Clustered Computing ቅድም እንዳልነው የተለያዩ ብዙ ኮምፒዩተሮች (PCs) በአንድ ኔትዎርክ ተገናኝተው አንድና ተመሳሳይ ስራ ሲሰሩ ነው። 'Cluster' ማለት እራሱ የተለያዩ (ተመሳሳይ) ነገሮች ስብስብ ማለት ነው። እንዲህ መሆኑ ጥቅሙ ምንድነው❓ 📍Resource Pooling: Combining the available storage space to hold data is a clear benefit. በCluster ጊዜ በምንጠቀማቸው ኮምፒውተሮች ውስጥ ያለውን የ'Storage' ስፍራ አንድ ላይ በማምጣት ዳታውን እንዲይዝ ማድረግ። 📍High Availability: provide varying levels of fault tolerance and availability guaranteed. የተለያዩ የሃርድዌር እና ሶፍትዌር ችግሮች እንዳይፈጠሩ አስቀድሞ ጥንቃቄ የሚያደርግ ነው። 📍Easy Scalability: Easy to scale horizontally by adding additional machines. በምንፈልገው አቅጣጫ መጠኑን (Sizeኡን) ማሳደግ እንችላለን። ማወቅ ያለብን ነገር ደግሞ "Cluster" ስንጠቀም፦ "Managing Cluster Membership, Coordinating resource sharing and Scheduling Actual work" እነዚህን ስራዎች የሚሰራልን ሶፍትዌር ያስፈልገናል። ይህንን ደግሞ እንደ "Hadoop's YARN" የመሳሰሉ ሶፍትዌሮችን መጠቀም ይቻላል። Hadoop ምንድነው❓

Course Hive

Continue this lesson in the app

Install CourseHive on Android or iOS to keep learning while you move.

Related Courses

FAQs

Course Hive
Download CourseHive
Keep learning anywhere